logo

BGRS held Conference on Pece

የበርታ ብሔረሰብ በምስራቃዊ ስናር/ሱዳን/ ግዛት የየገሪን የሚባለውን ተራራማ ሰፊ ግዛትና በኢትዮጵያ ውስጥ የአባይንና የዳቡስ ሸለቋማ አካባቢን ይዞ ለረጅም ጊዜ የኖረ ህዝብ ነው፡፡ ብሄረሰቡ ዛሬ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚገኙ አምስት ነባር ብሔረሰቦች አንዱ ሲሆን በአሶሳ ዞን ወረዳዎችና በበሎ ጅጋንፎይ ወረዳ በተለያየ ቦታ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ ከሚገኙት ሶስት የቋንቋ ግንዶች (ሰመቲክ፣ ኦሞቲክና ናይሎ ሳሃራ) ውስጥ የበርታ ብሔረሰብ ቋንቋ በናይሎ ሳሃራ ውስጥ ይመደባል፡፡ አልፎ አልፎ ከሚስተዋሉት የባህላዊና የአምልኮ ስርዓቶች ውጪ አብዛኛው የበርታ ህዝብ የእስልምና እምነት ተከታይ ነው፡፡ 18ኛው ክፍለ ዘመን የሲናሩ ፉኝ ግዛት በምስራቃዊ ሱዳን በኩል እስልምናን በቤኒሻንጉል ለማስፋፋት መነሳቱንና እምነቱ በበርታ ህዝብ ውስጥ መስረጽ መጀመሩ በታሪክ ይወሳል፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በበርታ ህዝብ ቱፊታዊ ህላዊና ዓመታዊ በዓላቱ ላይ የእምነቱ ጥላ ጎልቶ ይታያል፡፡ በበርታ በማህበራዊና ባህል ስርዓታቸው ውስጥ የሚታወቁበት የእንግዳ አቀባበል ስርዓታቸው ነው፡፡ በርታዎች እንግዳን ይወዳሉ፡፡ ያከብራሉ፡፡ እንግዳው ከየትም ይምጣ ሁሉም ለማስተናገድ ዝግጁ ናቸው፡፡ የዘመናት ታሪክና ባህል ባለቤት የሆነው የበርታ ብሔረሰብ አካባቢው ባለው ወርቅ ሀብት ምክንያት ከጥንታዊ ግብፃዊያንና አክሱማዊያን ጋር ግንኙነት እንደ ነበረው የታሪክ መዛግብት ያወሳሉ፡፡ ለግብፅ ፈርኦኖች፣ ለአክሱምና ለመረዌ ነገስታት የባሪያና የወርቅ ንግድ ምንጭ በመሆን ግንኙነት እንደ ነበረው የታሪክ መዛግብት ሲያውሱ የሩቅ ዘመኑን ብቻ ሳይሆን የቅርብ ጊዜ ታሪካችን የመዘገበው ይህንኑም የክልሉን የወርቅ ሀብት ክምችት የሚያሳይ እውነታ ነው፡፡

Image

አስተያየት ይስጡ

Comments


By |pHqghUme ( April 15, 2023 - 19:12:11pm)

555


By |pHqghUme ( April 15, 2023 - 19:12:10pm)

555


By |pHqghUme ( March 21, 2023 - 14:11:03pm)

555


By |pHqghUme ( March 21, 2023 - 14:10:05pm)

555


By |dfdf ( March 04, 2020 - 07:51:07am)

nnnnnnnnnnn


By |yi ( March 04, 2020 - 07:46:44am)

ghghghghghnnnnnnnnnnnn


By |Melkamu D. ( February 28, 2020 - 11:13:13am)

vbbv


By |Wublem ( December 08, 2019 - 10:45:46am)

Excellent work


By |Betelhem ( November 27, 2019 - 07:48:56am)

bbbbbbbbbbbbbbbbbbbbbbbbbbbbbbbbbnnnnnnnnnnnnnnn


By |Sisay M ( November 27, 2019 - 07:48:40am)

gggggggggggggggggg