logo






ስክልል ምክር ቤት ጽህፈት ቤት፣ - ተልዕኮ፣ራዕይና እሴቶች

የክልል ምክር ቤት ተልዕኮ፣ራዕይና እሴቶች

ራዕይ (Vission)

በሚቀጥሉት 20 ዓመታት የህግ የበላይነት ተረጋግጦ መልካም አስተዳደር ሰፍኖ ጠንካራ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መሰረት ተጥሎ የክልሉ ህዝብ የዘላቂ ልማት ተጠቃሚ ሆኖ ማየት፤

ተልዕኮ (Mission)

በክልሉ የተለያዩ ህጎችን በማውጣት የህጎችን አፈፃፀም በመከታተል ፣በመቆጣጠር፣ በመመርመርና የህዝብ ውክልናን በብቃት በመወጣት የህግ የበላይነት የተረጋገጠበትና መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ክልል ለመገንባት በቁርጠኝነት መስራት፤

የአሰራር ዕሴቶች /values/

1.በህግ አወጣጥ ሂደት ህዝቡን እንሳትፋለን፤
2.በህግ አፈፃፀም ሂደት ህዝቡን እናዳምጣለን፤
3.ቁጠባን መሰረት በማድረግ በእቅድ እንመራለን፤
4.ከምንም በላይ በህዝብ የስልጣን ባለቤትነት እናምናለን፤
5.የህዝብን አደራ በህዝባዊ ስሜት እንወጣለን፤
6.ራዕያችንን ዕውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንሰራለን፤

የም/ቤቱ ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት

ም/ቤቱ ህገ መንግስታዊ ኃላፊነቶቹን በአግባቡ መወጣት ይችል ዘንድ አስተዳደራዊና ሙያዊ ድጋፎችን የሚሰጠው የራሱ ጽ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 32/1995 በማቋቋም የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ሰጥቷል፤

1.ለም/ቤቱና ለአካላቱ የጽህፈት አገልግሎት ይሰጣል፤
2.ለም/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሾችን ያዘጋጃል፤
3.የም/ቤቱን ቃለ ጉባኤዎችንና የውሳኔ ሀሳቦችን ተመዝግበው እንዲያዙ ያደርጋል፤
4.የም/ቤቱ እንግዶች አስፈላጊውን መስተንግዶ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
5.በም/ቤቱ የሚጸድቁ አዋጆችን ያሳትማል ፣ያስራጫል ተፈፃሚነታቸውንም ክትትል ያደርጋል፣

አዳዲስ ተንቀሳቃሽ ምሽሎች
ሁሉንም ምሽሎች ተመልከት

መገኛ ካርታ