logo

የተሻሻለው የክልሉ ሕገመንግስት ስለ ስልጣን አካላትና ስለም/ቤት ምን ይደነግጋል ?

አንቀጽ 46 የክልሉ መንግስት የሥልጣን አካላት 1. የክልሉ መንግስት ሕግ አውጪ አካል የክልሉ ምክር ቤት ሲሆን የክልላዊ መንግስት ከፍተኛ የሥልጣን አካል ሆኖ ተጠሪነቱ ለወከለው ሕዝብ ነው፡፡ 2. የክልሉ ከፍተኛ የሕግ አስፈፃሚ አካል የክልሉ መስተዳደር ምክር ቤት ሲሆን ተጠሪነቱ ለክልሉ ምክር ቤት ነው፡፡ 3. የክልሉ የዳኝነት ሥልጣን የክልሉ ፍርድ ቤቶች ብቻ ነው፡፡ አንቀጽ 48 ስለክልሉ ምክር ቤት አባላት 1.የክልሉ ምክር ቤት አባላት ነፃ፣ቀጥተኛ፣ትክክለኛ በሆነና ድምጽ በምስጢር በሚሰጥበት ሥርዓት በየአምስት ዓመቱ በሕዝብ ይመረጣሉ፡፡ 2.የምክር ቤቱ አባላት በአንድ የምርጫ ክልል ውስጥ ከሌሎች ተወዳዳሪዎች መካከል አብላጫ ድምጽ ያገኘ ተወዳዳሪ አሸናፊ በሚሆንበት የምርጫ ሥርዓት ይመረጣሉ፡፡ የምክር ቤቱ አባላት ቁጥር የሕዝብ ብዛትን መሠረት ያደረገ ይሆናል፡፡ የማኦና የኮሞ ብሄረሰቦች ውክልና በልዩ ሁኔታ ይታያል፡፡ ጠቅላላ የክልሉ ምክር ቤት አባላት ቁጥር ከአንድ መቶ አይበልጥም፡፡ የተለየ ውክልና እንደሚያስፈልጋቸው የታመነባቸው ሕዝቦች በምርጫ ምክር ቤቱ ውስጥ ይወከላሉ፡፡ ዝርዝሩ በህግ ይወሰናል፡፡ 3.የምክር ቤቱ አባላት የመላው የክልሉ ሕዝብ ተወካዮች ናቸው፡፡ ተገዥነታቸውም፡- ሀ. ለሕገ መንግስቱ ለ. ለመረጣቸው ሕዝብና ሐ. ለራሳቸው ሕሊና ብቻ ይሆናል፡፡ 4.ማንኛምውም የምክር ቤቱ አባላት በምክር ቤቱ ውስጥ በሚሰጠው ድምፅ ወይም አስተያየት ምክንያት አይከሰስም፤ አስተዳደራዊ እርምጃም አይወሰድበትም፡፡ 5.ማንኛውም የምክር ቤት አባል ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለምክር ቤቱ ፍቃድ አይያዝም፤በወንጀልም አይከሰስም፡፡ 6.ማንኛውም የምክርቤቱ አባል የመረጠው ሕዝብ አመኔታ ባጣበት ጊዜ በሕግ መሰረት ከምክር ቤት አባልነቱ ይወገዳል ፡፡ 7.የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 6 ድንጋጌ እንደአግባብነቱ በየደረጃው በሚገኙ ምክር ቤቶች ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡ አንቀጽ ፵፱ የክልሉ ምክርቤት ስልጣንና ተግባር የክልሉ ምክር ቤት በተሻሻለዉ የክልሉ ህገ-መንግስት አንቀጽ 49 መሰረት የክልሉ ህግ አውጭ አካልና በዉስጥ ጉዳዮች ከፍተኛ የፖለቲካ ሥልጣን ባለቤት ሲሆን በህዝቡ የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት ለመወጣት የሚከተሉት ተግባራት ተለይተዉ ተሰጥተዉታል፡፡  የፌዴራሉን ህገ-መንግስትና ሌሎችን ህጎችን በማይፃረር ልዩ ልዩ ህጎችን ያወጣል፣  የህዝቡን ብዛት፣ የክልሉን ስፋትና ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ግምት ውስጥ በማስገባት በክልሉ ውስጥ ተጨማሪ የአስተዳደር እርከኖችን ወይም የራስን በራስ አስተዳደር አካባቢዎችን በህግ ያቋቁማል፣  የፌዴራል መንግስት ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ከአጎራባች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት ጋር የሚያደርጉ ስምምነቶችን ያፀደቃል፣  የራሱን አፈ-ጉባኤና ምክትል አፈ-ጉባኤ ይመርጣል፤ ለምክር ቤቱ ስራ የሚያሥፈልጉትን ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎችን ይሰይማል፤  ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ርዕስ መስተዳደሩን በምርጫ ይሰይማል፤ በርዕስ መስተዳደሩ አቅራቢነት ክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አባላት ሹመት ያጸድቃል፤  በርዕሰ መስተዳድሩ አቅራቢነት የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንት፤ ዋና ኦዲተሩንና ምክትል ዋና ኦዲተሩን ይሾማል፣  የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት፤ከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶችን ያቋቋማል፤ዳኞችን ይሾማል፣  የኦዲትና ሌሎችንም የቁጥጥር አካላትን ያቋቁማል፤  የክልሉን ሠላምና ፀጥታ ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ያወጣል፤ የፀጥታንና የፖሊስ ኃይሎችን ያቋቁማል፤  ክልሉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፕሮግራሞችን ያፀድቃል፤  የክልሉን የገቢ ምንጮችን የሚመለከቱ ህጎችን ያወጣል፤ የክልሉን በጀት ለብሄረሰብ ምክር ቤቶች፣ ለአስተዳደራዊ እርከኖችና ወረዳዎች በመቀመር ይመድባል፤ መርምሮ ያፀድቃል፡፡  ለማህበራዊ አገልግሎት መስፋፋት፤ ለኢኮኖሚ ልማት መፋጠንና ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ተቋማትን ያቋቁማል፤  ለክልሉ መንግስት በተከለለው የገቢ ምንጭ በክልሉ ውስጥ የግብርና ታክሲ ይጥላል፤  የክልል መስተዳደሩን ሰራተኛ አስተዳደርና የስራ ሁኔታዎችን በተመለከተ ህግ ያወጣል፤  ለክልሉ መንግስት በተሠጠዉ ስልጣን መሰረት የአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጣል፤  የሀገሪቱንና ክልሉ ህግጋተ መንግስታት አዋጆችና ሌሎች ህጎችን በክልሉ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ዝርዝር ማስፈፀሚያ ደንቦችን ያወጣል፤  የክልሉን ርዕስ መስተዳደርና ሌሎችንም የክልሉ መንግስት ባለስልጣናት ለጥያቄ ይጠራል፤ የአስፈፃሚውን አካል አሰራር ይመረምራል፡፡

አዳዲስ ተንቀሳቃሽ ምሽሎች
ሁሉንም ምሽሎች ተመልከት

መገኛ ካርታ