logo

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ለክልሉ የ2017 ማስፈጸሚያ የሚሆን ከ8 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ።

(ሐምሌ 21/2016 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ለክልሉ የ2017 ማስፈጸሚያ የሚሆን ከ8 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ። ምክር ቤቱ ለክልሉን የ2017 ማስፈጸሚያ የሚውል በጀት 8 ቢሊዮን 974 ሚሊዮን 531 ሺህ 586 ብር አጽድቋል። ለክልሉ ከተያዘው በጀት ውስጥ 3 ቢሊዮን 784 ሚሊዮን 430 ሺህ 733 ብሩ ከፌዴራል መንግስት በድጎማ የሚገኝ መሆኑ ተገልጿል። 4 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ብሩ በክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢ የሚሸፈን ሲሆን፣ ቀሪው ደግሞ ከተለያዩ የገቢ አማራጮች የሚገኝ መሆኑን የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዚያድ አብዱላሂ ገልጸዋል። በ2017 ለክልሉ የተያዘው በጀት ካለፈው 2016 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ6 በመቶ ዕድገት ማሳቱን ተናግረዋል። የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው፣ የህዝቡን የልማት ጥያቄዎችን በወቅቱ ለመመለስ በክልሉ ያሉትን ለገቢ የሚሆን ምቹ አቅሞች በመጠቀም የሚሰበሰበውን ገቢ እያሳደጉ መሄድ እንደሚጠበቅ አሳስበዋል። በበጀት ዓመቱ የተያዘውን በጀት በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በየደረጃው ክትትል ማድረግ ይጠበቃልም ብለዋል። የክልሉ ምክር ቤት በጀቱን ከመረመረ በኋላ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

Image

አስተያየት ይስጡ

Comments