logo

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 18ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

(ሐምሌ፤20/2016 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 5ኛ 5 ዓመት 10ኛ የሥራ ዘመን 18ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ማካሄድ ይጀምራል። ምክር ቤቱ በሀገራችን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በመሬት ናዳ ጉዳት ለደረሰባቸው ወጎኖች የኅሊና ጸሎት በማድረግ ነው ጉባኤውን የጀመረው። የምክር ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው ጉባኤ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የሚቀርበውን የክልሉ መንግስት የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በማድመጥ ውይይት ያደርጋል። በተጨማሪም የክልሉ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶችን በማድመጥ ይወያያል። በጉባኤው የክልሉን የ2017 በጀት ዓመት ማስፈጸሚያ በጀትን ጨምሮ በሚቀርቡ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል።

Image

አስተያየት ይስጡ

Comments