logo

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ለርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አሻድሊ ሀሰን ዕውቅና ሰጠ

(ሐምሌ 18/2015 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለተወጡት የመሪነት ሚና ዕውቅና ተሰጣቸው። ምክር ቤቱ ለርዕሰ መስተዳድሩ ዕውቅናውን የሰጣቸው ባለፉት ዓመታት በተሰጣቸው የሕዝብ ኃላፊነት ለተወጡት የመሪነት ሚና እና ክልሉ ለበርካታ ዓመታት ገጥሞት ከነበረው የፀጥታ ችግር በመውጣት ወደቀደመ ሠላሙ እንዲመለስ ላበረከቱት ያላሰለሰ ድርሻ ነው። የምክር ቤቱን ዕውቅና የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ዶ.ር ተመስገን ዲሳሳ እና ምክትል አፈጉባኤ ወ/ሮ ዓለምነሽ ይባስ ለተሸላሚው አበርክተዋል። ክቡር አቶ አሻድሊም ዕውቅናውን በተቀበሉበት ወቅት ሰው ሥራ ላይና በሕይወት እያለ ማመስገንና ዕውቅና መስጠት ባህል እየሆነ መምጣቱ የሚበረታታ እና ሊጠናከር የሚገባው ተግባር መሆኑን ጠቅሰው ዕውቅናው የክልሉ ሕዝብና አብረውኝ ለሠሩ ሁሉ የተበረከተ ነው በማለት በክልሉ ምክር ቤት ለተሠጣቸው ስጦታ የከበረ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ዕውቅናው ለቀጣይ ከህዝቡ ጋር የበለጠ ተቀራርቦ በመሥራት ያልተሻገርናቸውን ችግሮች በጋራ በመሻገር ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲንረባረብ ስለሚያነሳሳ እርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። ያገኘናቸው ስኬቶች እንደተጠበቁ ሆነው፣ አሁንም ህዝቡን ከድህነት ለማውጣት መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል ሲሉም አክለዋል። ዕውቅናውን ካበረከቱት መካከል ም/አፈጉባኤ ወ/ሮ ዓለምነሽ ይባስ በዚሁ ወቅት አቶ በወጣትነት ዕድሜያቸው እንደሰው ማረፍና ቤተሰባቸው ጋር መሆን ሳያምራቸው የህዝብ ኃላፊነትና ተጠቃሚነት ይበልጣል በማለት እራሳውን የሰጡ መሪ በመሆናቸው እኛም በእርሳቸው በመመራታችን ዕድለኞች ያስብለናል፡፡ የተሰጣቸውም ዕውቅና ቢያንስባቸው እንጂ አይበዛባቸውም ብለዋል፡፡

Image

አስተያየት ይስጡ

Comments


By |Smith ( January 05, 2024 - 08:07:27am)

3


By | ( January 05, 2024 - 08:07:24am)