logo

news2

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ም/ቤት የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ጉባዔውን አጠናቀቀ ************** የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት በ13ኛ መደበኛ ጉባዔው የተለያዩ ውሳኔዎችን እና አዋጆችን በማፅደቅ ጉባዔውን አጠናቋል፡፡ የክልሉ ምክር ቤት የክልሉን ያልተማከለ የወረዳ አካባቢ አስተዳደርን ለማጠናከር የቀረበውን የማሻሻያ አዋጅ በመመርመር የአሶሳ ወረዳ በሁለት ወረዳዎች እንዲዋቀር አጽድቋል፡፡ በማሻሻያ አዋጁም አሶሳ ወረዳ የሚለው ቀርቶ "ኡራ ወረዳ" እና "አብርሃሞ ወረዳ" ተብሎ በሁለት ወረዳዎች መዋቅሩ ተገልጿል፡፡ በዚህም ለህዝብ አስተዳደር በሚመች መልኩ ኡራ ወረዳ 41 እንዲሁም አብርሃሞ ወረዳ ደግሞ 41 ቀበሌዎችን እንዲኖሯቸው ተደርገው መደራጀታቸውን ከክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡ ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪ በቀደመው ጊዜ በርታ ተብሎ ሲጠራ የነበረውን የብሔረሰብ መጠሪያ "ቤኒሻንጉል" ተብሎ እንዲሰየም የቀረበለትን የብሔረሰብ መጠሪያ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡ ምክር ቤቱ ከዚህ ባለፈ የቤንሻጉል ጉሙዝ ክልል ሚሊሻ ጽ/ቤትን እንደገና ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ ላይ ተወያይቶ በማጽደቅ 13ኛ መደበኛ ጉባዔውን አጠናቋል።

Image

አስተያየት ይስጡ

Comments


By | ( November 16, 2022 - 03:07:06am)



By |Smith ( November 16, 2022 - 03:07:06am)

3


By |Smith ( November 15, 2022 - 13:06:47pm)

3


By | ( November 15, 2022 - 13:06:45pm)



By | ( November 15, 2022 - 10:47:49am)



By | ( November 15, 2022 - 09:54:21am)



By | ( November 14, 2022 - 16:37:04pm)